ለፋብሪካው የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የእውቅና ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የፍይናንስ መምሪያ 2016 በጀት ዓመት ሒሳብ በፋሪካው ታሪክ ከረጅም ዓመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሒሳብ ነሀሴ 24 /2016 ዓም በመዝጋታቸው እና ያለፋ ዓመታት የኦዲት ግኝቶች ላይ በአጭር ጊዜ ማስተካከያ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሠራተኞች እና ሀላፊዎች እውቅና እና ሽልማት በቢሾፍቱ ከተማ ኖራ ሪዞርት ተከናውኗል ።
የፍይናንስ መምሪያ ሒሳብ በወቅቱ እንዲዘጋ እና ሌሎች ሥራዎች እንዲከናውን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉት ከ 22 አመት በፊት በፍብሪካው የፋይናንስ ሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ የነበሩ እና ለ 22 ዓመታት በአሜሪካ እና በተለያዩ ሀገራት ብሎም በአለም አቀፍ ተቋማት በፍይናንስ ሀላፊነት ያገለገሉ አቶ ለቤዛ አለሙ ናቸዉ ።
የፍብሪካዉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን አቶ ለቤዛ አለሙ የፍይናንስ አሠራር ወደ ተሻለ አፈጻጸም እንዲመጣ ላደረጉት ድጋፍ ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል። አክለውም በየደረጃው ላሉ የፋይናንስ ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበው የእውቅና እና ሽልማት ተሠጥቷቸዋል።