በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ለአባትና እናት ጡረተኞች የሸኝት መርሃ-ግብር ተካሄደ
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ ለረዥም ዓመታት በታማኝነት እና በቅንነት ሲያገለግሉ ቆይተው በዕድሜ ጣሪያ ምክንያት ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ የተሰናበቱ እናት እና አባት ጡረተኞች በወንጂ የሠራተኞች መዝናኛ ከበብ ሽኝት ተደረገላቸው፡፡
የዘንድሮው የሽኝት መርሃ-ግብር ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው ፋብሪካው ሌሎች አምስት ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ በመንግስት በተላለፈ ውሳኔ መሰረት የስራ አመራር ቦርድ ተቋቁሞለት እራሱን ችሎ እንዲመራ በተወሰነ ማግስት መሆኑና በአዲስ ምዕራፍ የተለያዩ ስትራተጂዎችን ነድፎ ወደ ቀድሞ አቋሙ ለመመለስ በሚደረግ የባለሙያዎች ርብርብ እና የቅርብ ክትትል አመራር እየተሰጠ ባለበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡
በዚህም የሽኝት መርሃ-ግብር የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን፣ የኢትዮጲያ የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ተወካይ አቶ ገበየሁ ማስረሻ እና ሌሎች አመራሮች ለጡረተኞቹ የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸዋል፡፡