በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በወንጂ አካባቢ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ኃ/የተወሰነ መካከል ለ3 ዓመታት የሚያገለግል 12ኛው የሸንኮራ አገዳ የመሸጥና የመግዛት የውል ድርድር ስምምነት ተጠናቆ የሰነድ ርክክብ ተደረገ፡፡
ይህ የውል ስምምነት ከዚህ በፊት የነበሩት ስምምነቶች ላይ ያሉትን ክፍተቶች በሁለቱም ወገን ጊዜ ሰጥቶ በሚገባ በመፈተሽ ከሌላው ጊዜ በደንብ ተጠንቶ እና ተሻሽሎ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ መሆኑንና ለተግባራዊነቱ በሁለቱም ወገን ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩበት በርክክብ ሂደቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ይህንንም የውል ስምምነት ሰነድ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን እና የዩኒየን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ንጉሴ ሚደቅሶ በመፈራረም ርክክብ አድርገዋል፡፡