በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የምርምርና ስርፀት አገልግሎት ስራ ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡

በተለያየ ጊዜ ከውጭ አገር እና ከአገር ውስጥ የተሰበሰቡ 1413 የሚደርሱ ብዘሀ ዘር (Geno types) በፋብሪካው 3 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማሳ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ የምርምርና ጥናት ስራ በምርምርና ስርፀት አገልግሎት ክፍል አማካይነት የስራ ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡

ከተሰበሰቡት 1413 ብዘሀ ዘር በተለያየ ጊዜ ምርምርና ጥናት ተደርጎባቸውና ተገምግመው የተለዩና የተሻሻሉትን 8 ዝርያዎች የዘር ብዜት በመተግበርና በቀጣይ ወደ ምርት ሂደት በማስገባት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችል አበራታች ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ቀደም ብለው የተለቀቁትን 16 ዝርያዎች የመቁረጫ ዕድሜ (Harvesting age) ከ14-22 ወር የሚውስን የምርምር ሙከራ በሂደት ላይ እንዳለ ተገምግሟል፡፡

በተጨማሪም የመስኖ ውሀ አጠቃቀምን በተመለከተ ከዚህ በፊት ሙሉ ማሳ በመስኖ ውሃ የሚጠጣ ሲሆን አሁን ግን በጥናት ቦዮችን በማፈራረቅ የተመጣጠነ ውሀ በማጠጣት፤ ወጪን በመቀነስ ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንደሚያስችል በመስክ ምልከታው ወቅት ተገልጿል፡፡  በቀጣይም የሸንኮራ አገዳ ማሳዎችን ሳተላይት ቴክኖሎጂ በመጠቀም መከታተል እነደሚቻል ቅድመ ሁኔታዎች የተጠናቀቁ መሆኑን የምርምርና ስልጠና ዘርፍ እና የምርምርና ስርፀት አገልግሎት ተመራማሪዎች በሰፊው አብራርተዋል፡፡

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Exit mobile version