የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር አካል የሆነዉ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ስነስርአት እንደ ተቋም መንከባከብ የእኔም ግዴታ ነዉ በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናወነ፡፡በእለቱ የፋብሪካዉ ዋና ስራአስኪያጅ የሆኑት አቶ ጀማል አማን እንዲሁም የዘርፍ ስራአስኪጆችን ጨምሮ በየደረጃዉ ያሉ የስራ ሃላፊዎችና የፋብሪካዉ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ከወንጂ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊና የቀበሌ አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡በመርሃግብሩ ላይ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለተሰታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት ዛፍ በመትከላችን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀመሜታ አግኝተናል ብለዉ ችግኝ መትከል ብቻዉን ግብ እንዳልሆነና መንከባከብ እንደሚገባ በመግለፅ በቀጣይ 2017 ዓ.ም ምርት ዘመን እንደ ፋብሪካችን የተያዘዉን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የስራ ሃላፊና ሰራተኛ የበኩሉን ሚና መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በፋብሪካ ደረጃ ከ100ሺ በላይ የፍራፍሬ ፣ ቀርክሃ እና ለግንባታ የሚሆኑ ዛፎች ችግኝ ተከላ እንደሚከናወንና በዛሬዉ መርሃግብር በወንጂና ሸዋ ላይ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ ተከታታይ ቀናት በፋብሪካ እና በየመኖሪ ሰፈሮች እንደሚቀጥል ከወጣዉ መርሃግብር ለመረዳት ይቻላል፡፡