‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ ማንነት!!!

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በፋብሪካው ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ ለተሰናበቱ እናትና አባት ጡረተኞች አሸኛኘት አደረገ።በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ በ2018 ዓ.ም በቁጥር 77 ለሚሆኑ ጡረተኞች አሸኛኘት የተደረገ ሲሆን 6ቱ ሴቶች መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል ።በዚህ ደማቅ መርሃግብር ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ እናንተ ዛሬ ለዚህ ክብር የበቃችሁ እንኳን አደረሳችሁ ብለው ፋብሪካው ያሳለፈው ውጣ ውረድ ቀላል እንዳልነበር አንስተው ያንን ፈተና ተቋቁማችሁ ፋብሪካውን ማሻገር በመቻላችሁ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል ። በመርሃግብሩ የፋብሪካው የሰው ሀብት ስራ አመራርና አቅርቦት ዘርፍ ስራአስኪያጅ አቶ አወል ሁሴን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የፌዴራል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ተወካይን ጨምሮ የፋብሪካው ሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ሊቀመንበር እንዲሁም የጡረተኞች ተወካይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በስነስርአቱ ላይ አባትና እናት ጡረተኞች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የታደሙ ሲሆን በፋብሪካ የቆይታ ግዜያቸው ላበረከቱት አስተዋጽዖ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል በዝግጅቱ መደ ሰታቸውንም ገልጸዋል።

Exit mobile version