አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል ::
ፋብሪካዉ መጋቢት 11 ቀን 1946 ዓ.ም ሆላንድ ቬንዴሪንግ አምስተርዳም በተባለ አለም አቀፍ ካምፓኒ ስኳርን እና ጣፋጭ ከረሜላ ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ በአገሪቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ዕድገት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ በማበርከት ላለፉት 70 ዓመታት በማምረት ሂደት ውስጥ አሳልፏል፡፡
የፋብሪካውን የ70ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በዕለቱ በተዘጋጀ ፕሮግራም መሠረት የፋብሪካዉን አርማ በክብር የመስቀል ፣ የተቸገሩ ወገኖች ማዕድ ማጋራት እንዲሁም አመሻሽ ላይ ለሙስሊም የህበረተሰብ ክፍል አፍጥር መርሀሃግብር በደማቅ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ፤
በእለቱ በፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን በፌዴራል ፖሊስ እና የደህነትና ንብረት ጥበቃ ታጅበዉ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አርማ የመስቀል ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን ይህን ተከትሎ ባስተላለፉት መልእክት ፋብሪካዉ አንጋፋ እንደ መሆኑ የፋሪካዉ ማህበረሰብ ታሪክን የሚናገር ብቻ ሳይሆን ታሪክ የሚሰራ እንደሆነ አንስተዉ የተያዘዉን የለዉጥ እንቅስቃሴ አጠናቅሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ለተደረገዉ ሁለንተናዊ ድጋፍም የፋብሪካዉን ስራ አመራር ቦርድ አመስግነዋል፡፡ በተመሳሳይ የወንጂ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቁምቢ ሎንገሌም ባስተላለፉት መልእክት ፋብሪካዉን የብዙ ሰዎች አባት እንደሆነ ገልጸዉ በቀጣይም ወደ ከፍታ ለሚያደርገዉ ጉዞ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል በተያያዘም ከወንጂ ወረዳ 6 ዞኖች ለተወጣጡ ለ100 አቅመ ዳካማ እና አረጋዉያን ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተከናዉኗል፡፡
አመሻሽ ላይም በተደረገው የአፍጥር መርሃ ግብር በፋብሪካዉ ክልልና አጎራባች ቀበሌ ጥሪ የተደረገላቸዉ የእስልምና ዓይማኖት እምነት አባቶችና ከተለያዩ እምነት የተወጣጡ የፋብሪካው ሥራ መሪዎችና ሰራተኖች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ተሳትፈዋል ፡፡
በተከናወኑ የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ወ/ሮ እታገኝ ጉርማሞ ንግግር የተደረገ ሲሆን የኢ.ስ.ኢ. ግሩፕ የምርምርና ስልጠና ዘርፍና የግሩፑ ተወካይ ጨምሮ፣ የፋብሪካዉ ከፍተኛ አመራሮች፣የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ስራአስፈጻሚዎች እንዲሁም የፋብሪካዉ ሰተኞችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል ፡፡ የወንጂ አጸ/ህ/1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችም ለፋብሪካዉ 70ኛ አመት የተዘጋጀዉን መዝሙር አቅረበዋል፡፡