ከሸንኮራ አገዳ ማምረት ልማት ውስጥ ወጥተው ከነበሩ አርሶ አደሮች ጋር ወደ ልማት ለመመለስ የመስክ ምልከታ እና ውይይት ተደረገ፡፡
መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም የፋብሪካዉ ከፍተኛ አመራር ከአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳደርና ከወንጂ አ/ሸ/አ/አ/ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አርሶአደሮች ጋር ዉይይትና መስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡
የመስክ ምልከታው እና ዉይይቱ በቀድሞው ምስራቅ ሸዋ ዞን በአሁኑ መዋቅር በአዳማ ከተማ አስተዳደር ሥር የታቀፉ የአዋሽ መልካሳ ወረዳ ስር ያሉ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ የነበሩ እና በተለያዩ ምክንያቶች ከአዉትግሮወርስ የሸንኮራ አገዳ ልማት የወጡ አርሶ አደሮችን ወደ ልማቱ ለመመለስ እንዲቻል ታስቦ በዶዶታ ክላስተር የለማ የሸንኮራ አገዳ ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ነዉ ፡፡
በመርሃ ግብሩ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን፣የአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደረጀ እና የዶዶታ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ አብደላ ጠደቻ ዉይይቱን በጋራ የመሩት ሲሆን የአዉትግሮወርስ ልማቱን የተመለከቱ ጥያቄና አስተያየቶች ከተሳታፊ አርሶ አደሮች ተነስተዉ በአመራሮች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል በተለይ አርሶአደሩ ወደ ሸንኮራ ልማቱ እንዲመጣ በፋሪካዉና ዩኒየኑ መካከል የተደረገዉ 12ኛ ዉል ስምምነት አርሶአደሩን ይበልጥ የሚያበረታታ እንደሆነ እንዲሁም በዶዶታ ክላስተር የለማው አገዳ ከፍተኛ ምርት እንደሚሰጥ የሚጠበቅ እና አርሶ አደሩን የበለጠ ተጠቃሚ እንደያደርገው ከተሳታፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡
በመርሃግብሩ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣የአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳደርና የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ፣የዶዶታ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ፣የወንጂ አካባቢ ሸ/አ/አ/ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ከፍተኛ አመራሮች፣ከዶዶታ እና አዋሽ መልካሳ ወረዳ አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን በመጨረሻም አርሶአደሮችን ወደ ልማቱ ለመመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዋሽ መልካሳ ወረዳ በኩል ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር መነጋገር እንዲቻል አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባዉ ተጠናቋል፡፡