የኢትዮጵያ ስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ አመራር፣የጣና በለስ፣የአርጆ ዴዴሳ፣ኦሞ ኩራዝ፣ፊንጫዓ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራእኪያጆች፣የገደብ ኢንጂነሪንግ እና የጆህንዲር ካምፓኒ የባለሙያዎች ቡድን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ለእንግዶች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በፋብሪካዉ የሚኖራቸዉ ቆይታ ያማረ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ ጉብኝቱ በዋናነት በጆህንዲር ካምፓኒ ምርቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ምርቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ፣በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች፣በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች ከተለያዩ የፋብሪካዉ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጥያቄና ሃሳብ ቀርቦ ከተለያዩ አህጉራት ከተወጣጡ የጆህንዲር ባለሙያዎች ምላሽና ገንቢ የሆነ ሙያዊ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የመስክ መሳሪያዎች ጥገና መምሪያ /ጋራዥ/ ፣ፋብሪኬሽን ወርክ ሾፕ ፣ በእርሻ ስራ ላይ ያሉ የጆህንዲር ማሽኖች እና በዶዶታ ወረዳ በአርሶአደሮች እየለማ የሚገኝ የሸንኮራ አገዳ ማሳ የተጎበኘ ሲሆን ከመስክ ምልከታዉ በኋላ ጎብኚዎች በተደረገላቸዉ አቀባበል ፣በመስክ ምልከታዉ መደሰታቸዉን እንዲሁም ሃሳቦችን በመለዋውጣቸዉ ለቀጣይ ስራ ጥሩ ግብዓት ማግኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version