የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወሎ አብዲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በፋብሪካዉ የመስክ ምልከታና የ6ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አደረጉ፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወሎ አብዲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በፋብሪካዉ የመስክ ምልከታና የ6ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አደረጉ፡፡
በመርሃግብሩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወሎ አብዲ፣የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ፣የኢ/ኢ/ሆልዲንግስ ም/ስራ አስፈጻሚዎች፣የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከዲርና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪጅጆችና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የፋብሪካዉ የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር አመራሮች በፋብሪካዉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ የፋብሪካዉ የ6 ወራት አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡
በወቅቱም የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለአብነት የኮሪደር ልማት ስራ፣ የእርሻ ዘርፍ የኦፕሬሽን ስራዎች፣የተጓዳኝ ልማት ስራዎች፣የአዉትግሮወርስ ልማት እመንዲሁም በፋብሪካዉ ዘርፍ የስኳር ምርት ስራን አስመልክቶ ለስራ ሃላፊዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በፋብሪካዉ እየተከናወነ ያለዉ የሪፎርም ስራ የያዘዉን ግለት ሳይለቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና የፋብሪካዉን አቅም ማሳደግ ፣ የሰራተኞች ሞራል ማስጠበቅ እንደሚገባ፣ የስኳር ባህል ማስጠበቅ፣ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር ያለዉ ግንኙነትና ፋብሪካው የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ፣አርሶአደሮችን ወደ ልማት ማስገባት ላይ እንዲሰራ እና እንደ አጠቃላይ ፋሪካዉ ለሌሎች ስኳር ፋብሪካዎች እንደ ምሳሌ የሚነሳ መሆኑን በማንሳት በኢ/ኢ/ሆልዲንግስ በኩልም አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎች እንደሚደረጉ በዋና ስራ አስፈጻሚዉ ዶ/ር ብሩክ ታዬ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
Exit mobile version