የወንጂ ገፈርሳ ከተማ አስተዳደር እና የወንጂ ገፈርሳ ቀበሌ ፅ/ቤት በወንጂ ሁለገብ እስታዲየም በጋራ ባዘጋጁት የወንጂ ገፈርሳ ከተማ የመሰረተ ልማት ስራ የገቢ ማሰባሰቢያ የሕዝብ ለሕዝብ ባዛር ዝግጅት ላይ በመገኘት የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ለአካባቢው ማህበረሰብ እና ለአጎራባች ቀበሌዎች ከማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚያደርጋቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለመሰረተ ልማት ስራው የሚሆን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
በቀጣይም የመንገድ ስራው ሲጀመር በማሽነሪም ሆነ ለመንገድ ስራው አስፈላጊ በሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ በማድረግ ፋብሪካው ከጎናቸው እንደሚሆን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን፣ የመምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጆች እና የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር አመራሮች በዕለቱ በአካል በመገኘት ቃል ገብተዋል፡፡     
Exit mobile version