የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በግብር ከፋይነት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ ::

በሀገር ደረጃ በተዘጋጀው የ6ኛው የታማኝ የግብር ከፋዮች ሽልማት በ 2016 በጀት ዓመት ፋብሪካው ለከፈለው ግብር መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ፡ም የገቢዎች ሚንስቴር በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ባዘጋጀው የእውቅና እና የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ፋብሪካው የብር ሜዳለያ ተሸላሚ በመሆኑ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ፋብሪካው በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን ሲያከናውን እንደነበር እና በ 2017 በጀት ዓመት የ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በማምረት ፋብሪካውን ወደ ቀድሞ የምርታማነት ልዕልናው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አበክረን እየጠየቅን በቀጣይ ዓመት ከምናመርተው ስኳር እና ተጓዳኝ ምርት ከፍተኛ ሽያጭ በማከናወን ለሀገራችን ብልጽግና የበኩላችንን አበርክተን በግብር ክፍያ የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ እንደምንሆን ሙሉ እምነት አለን ፡፡

Exit mobile version