የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 496/2014 መሰረት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ለመላቀቅ እንዲያስችል ተቋማዊ የሪፎርም ፕሮግራሞችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋናነት በአዲስ መልክ የተሻሻለውን የሰው ሀብት አደረጃጀት ድርጅታዊ መዋቅር፣ የሠራተኞች የስራ ምደባ አፈፃፀም መመሪያ፣ በትግበራው ተስፋ ሰጪ በሆኑ ተጨባጭ የውጤት ማሳያዎች እና በተፈጠሩ የልማት ተግዳሮቶች ላይ ስትራቴጂ ነድፎ ሠራተኛውን ግንዛቤ በማስጨበጥ በተቋማዊ የገፅታ ግንባታ እና በሠራተኛው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ውይይት አደረገ፡፡
በተጨማሪም የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ባስተላለፉት መልዕክት በመከናወን ላይ ባለው ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ፕሮግራም የስራ ሀላፊዎች እና የማህበር አመራሮች ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው ተገቢውን ሠራተኛ ለተገቢው ቦታ በመስጠት በታሪክ አጋጣሚ የተሰጣቸውን የሀላፊነት ሚና በመጠቀም ተቋሙን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያሻግር መሆን እንዳለበት ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡