የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አዲስ የሰው ሀብት አደረጃጀት መዋቅር ለመተግበር ግንዛቤ የመፍጠር ውይይት አደረገ፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 496/2014 መሰረት ራሱን ችሎ እንዲቋቋምና በቦርድ እንዲመራ በመደረጉ የመጀመሪያውን አዲስ የተሸሻለ የሰው ሀብት አደረጃጀት ድርጅታዊ መዋቅር እና የሠራተኞች የስራ ምደባ አፈፃፀም መመሪያን አስመልክቶ ለፋብሪካው ማኔጅመንት እና ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር አመራሮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ውይይት አደረገ፡፡
ይህንንም የሠራተኞች የመልሶ ምደባ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ የተገባና የለውጡን ዓላማ ታሳቢ በማድረግ ተቋሙን ወደነበረበት አቅም ለማሻገር የተነደፈውን ስትራተጂ ለማሳካት በመከናወን ላይ ባለው ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ፕሮግራም የሚመለከታቸው አካላት ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው ተገቢውን ሠራተኛ ለተገቢው ቦታ በመመደብ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡       
Exit mobile version