የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከባንክ ብድር እንዲመቻችለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የአዋጭነት ጥናት ሰነድ እንዲያቀርቡ ሰነድ ተፈራረሙ ፡፡

የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሀገሪቱን የስˆር ፍላጎት በማሟላት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስኳር እና የተጓዳኝ ምርት በአነስተኛ የማምረቻ ወጪ በማምረት ትርፋማ እና ተወዳዳሪ ስኳር ፋብሪካ ማድረግ ራእይው አድርጎ የተነሳ ሲሆን በቀጣይም የፋይናንስ አቅሙን በማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ለመስራት አቅዷል ፡፡የመንግስት ልዩ ትክረት ያልተለየው የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ያጋጠመውን የፋይናንስ ምንጭ እጥረት ለመቅረፍ እና የተጀመረውን የፋብሪካውን ተሃድሶ እና መልሶ ግንባታ ስራዎች ማለትም በድሬኔጅ ችግር ምክንያት በውሀ ተበልተው ሸንኮራ አገዳ ሳይለማባቸው የቆዩ ማሳዎች ወደ ልማት መመለስ፣የምርታማነት ችግር ያለባቸውን ማሳዎች ከድሬን ላይ በሚነሳ አፈር የማከም ስራ በሚፈለገው ልክ ለመሰራት፣የግብዓት አቅርቦትና መለዋዋጫ እጥረቶችን ለመቅረፍ፣ የፋብሪካ ተርባይንን ጠግኖ ወደ ስራ በማስገባት በየዓመቱ በሚሊየኖች የሚወጣውን ከፋተኛ የኤሌክትሪካ ወጪ ለመቀነስ ፣ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ማሽኖችና ተቀጽላዎችን ለመተካት እና ዋና ዋና የፋብሪካው ማነቆ የሆኑትን ችግሮች ለመቅረፍ ከባንኮች ብድር እንዲመቻችለት የአዋጭነት ጥናት ሰነድ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተጠንቶ ለባንኮች እንዲቀርብ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ጋር ጳጉሜ 3/2015 ዓ.ም የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡

Scroll to Top