በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በየዓመቱ በምርት ዘመኑ መጨረሻ ክረምት ላይ የሚካሄደው የቤተሰብ ስፖርት ውድድር ሰራተኛው፣ ቤተሰቡ እና ስፖርት ወዳዱ የወንጂ አካባቢ ኅብረተሰብ በታደሙበት ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በወንጂ ሁለገብ ስቴዲየም ተጀመረ፡፡
በውድድሩ ላይ የተገኙት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን እና የወንጂ ሸዋ እና ተክል ክፍል መሰረታዊ ሰራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ዶሎና የውድድሩን መጀመር አስመልከቶ ስፖርት ለሰራተኛው ጤንነት የአካልና የአዕምሮ ዕድገት ብሎም ለምርታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመግለጽ በቀጣይ የምርት ዘመን የያዝናቸውን ዕቅዶች ከግብ ለማድረስ በተሰማራንበት የሥራ መስክ እጅ ለእጅ ተያይዘን በባለቤትነት መንፈስ ሰርተን ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል በማለት ጫዋታውን በስፖርታዊ ዲስፕሊን ላይ ተመርኩዛችሁ በጨዋነት መንፈስ እንድትጫወቱና እንድትከታተሉ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ውድድሩ መጀመሩን በይፋ አብስረዋል ፡፡
የመክፈቻ ጫዋታውም በፋብሪካው ማኔጅመንት እና የመሰረታዊ ሰራተኛ ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል ውድድር ተደርጎ ታዳሚውን በማስደሰት እና በማዝናናት ከተጫወቱ በኋላ በዕለቱ በመደበኛነት የመስክ መሳሪያዎች ጥገና መምሪያ ሰራተኞች ስፖርት ቡድን ከአገዳ ተከላና እንክብካቤ መምሪያ ሰራተኞች ስፖርት ቡድን ጋር የዓመቱን ውድድር በስፖርታዊ ጨዋነት መጫወት ተጀምሯል ፡፡