ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን አስቻይ ሁኔታዎችና የመልማት አቅም አሟጦ በመጠቀም ገቢዉን ለማሳደግ በተነደፈ ስትራቴጂ መሰረት የማምረት ስራዉን አቋርጦ የነበረዉን የፋብሪካዉን ታሪካዊ ምርት ደስታ ከረሜላን ዳግም ወደ ምርት ለመመለስ የአዋጭነት ጥናት ቀርቦ ወደ ቀጣይ ተግባራዊ ስራ ለመግባት የሚያስችል ዉይይት ተደርጓል፡፡
ደስታ ከረሜላ ወደ ምርት ቢገባ የፋብሪካዉን ታሪክ ዳግም በመጻፍ የነበረዉን የማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠቱም ባሻገር ማህበራዊ እርካታ በመፍጠር ተጨማሪ የስራ እድል የሚፈጥርና የሚያጓጓ ተጨማሪ ገቢ በማስገኘት ስኳር ፋብሪካዉን እንደሚደጉም እና ትርፋማነቱም በማኔጅመንቱ ታምኖበታል፡፡
ስለሆነም ፋብሪካዉን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ ቀጣይ ተግባራት እንዲፈፀሙ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
Exit mobile version