ፋብሪካዉ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲዩት ጋር IS0 9001 - 2015 ለማስጀመር ስምምነት ተፈራረመ

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አሰራሩን በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ለመፈጸም የሚያስችለዉን  እና ፋብሪካውም በቀጣይ ምርቱን በገበያ ላይ አቅርቦ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችለውን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ISO 9001–2015 ትግበራ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የሚያስችል ሥምምነት ሠነድ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲውት ጋር ተፈራርሟል፡፡

የስምምነት ሠነዱን የተፈራረሙት የወንጂ/ሸዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲውት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ ናቸው፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲውት ፋብሪካው የጥራት ስራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር እና የእውቅና ሰርተፍኬት ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት ላይ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅም ትግበራውን እስከ ታችኛው ሠራተኛ ድረስ በማዉረድ በአጭር ጊዜ መስፈርቱን አሟልተው የእውቅና ሰርተፊኬት በማግኘት የፋብሪካውን ምርት እና አገልግሎት ወደ አለም አቀፍ ስታንዳርድ ለማምጣት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

Scroll to Top