ፋብሪካዉ የ2017 ዓ.ም የ 1 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ምርት ለማሳካት የሚያስችል አገዳ መፍጨት ጀመረ፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የ2017 ዓ.ም ምርት ዘመን የ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት የሚያስችለውን  የሸንኮራ አገደ መፍጨት ጥቅምት 20 ቀን 2017 ከጠዋቱ 12፡00 ሠዓት  ሁሉም የስራ መሪዎች እና ሠራቸኞች በተገኙበት በተለያዪ ዘግጅቶች በደማቅ ሁኔታ በይፋ ጀምሯል፡፡

በትላንትናው እለት የተቆረጠውን አገዳ ከማሳ ተጓጉዞ ከቀረበ በኋላ የመጀመሪያውን ትራክተር ወደ ፋብሪካው ያስገቡት የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ፣የፋብሪካዉ ሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ሊቀመንበር

ወ/ሮ እታገኝ ጉርማሞ እና የፋብሪካ ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ሰገድ ተሾመ  እንዲሁም የእርሻ ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ኦቶ ሰለሞን በቀለ በጋራ ከጋሪ ላይ ወደ ብራንኮ ከገለበጡ በኋላ የኦፕሬሽን ሥራው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡ በፋብሪካው ማስጀመሪያው ወቅት የፋብሪካው  የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የፋብሪካ ማስጀመሪያ ሥነሥርዓቱ በፋብሪካው ህዝብ ግንኙነት ክፍል በተዘጋጀ መዝሙር እና ድራማ በማቅረብ እንዲሁም በጧፍ ማብራት ሥነ ሥርዓት በማድመቅ የሴቶች እና ወጣቶች አምባሳደሮች ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡

Scroll to Top