13ኛው ዙር የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና የወንጂ አካባቢ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የሸንኮራ አገዳ የማምረት የመሸጥና የመግዛት ውል የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናወነ፡፡

ለ50 አመታት የዘለቀው የሁለትዮሽ የልማት ትስስር በየሶስት አመቱ በሚታደስ ውል ዛሬ ለ13ኛጊዜ በይፋ በተደረገ ፊርማ ስነ ስርዓት የወንጂ ሸዋ ፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ የስራ አመራሮች፣ የህብረት ስራ ዩኒየኑ የቦርድ አባላት፣ የወንጂ ሸዋ ተክል ክፍል ሰራተኞች መሠረታዊ ማህበር አመራር፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሸንኮራ አብቃይ ማህበራት የተወከሉ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል።
‎መርሃ ግብሩ በሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በዕለቱም የምስራቅ ሸዋ ዞን የህብረት ስራዎች ማስፋፊያ ኤጀንሲ ተወካይ እና አደራዳሪ የነበሩት አቶ ኮርሜ ቡጳ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ በማለት የደስታ መልዕክት ካስተለላፉ በኋላ የሁለትዮሽ ጥቅምን መሠረት ያደረገና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሸንኮራ አገዳ ምርት ሽያጭና ግዢ ዉል ባማረ ሁኔታ መከናወን መቻሉን ገልጸዉ ‎ዉሉ ከመፈረሙ አስቀድሞ በሰለጠነ መልኩ ከሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎች ሃሳብን በነፃነት ሲንሸራሸር እንደነበር በመግለፅ በስምምነቱ ላይ መካተት የሚገባቸውን ነጥቦች መግባባት ላይ በመድረስ ለዛሬ የመጨረሻዋ የስምምነት ፊርማ ቀን የደረሱበት ነው ብለዉ ተግባራዊነቱም ሁለቱም ወገን እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
 
የዉል ፊርማ ስነስርአቱ ከተከናወነ በኋላም ‎የወንጂ አካባቢ ሸ/አ/አ/ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ባይሳ ሻምቡ ባስተላለፉት መልዕክት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የድርድር ሂደቱ ካለፉት የዉሉ ዘመናት የተሻለ እንደነበር ገልጸዉ በሸንኮራ አገዳ ምርትና ምርታማነት ይበልጥ እንዲሻሻል በመስራት አርሶአደሩ የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆን የበኩላቸዉን እንደሚወጡ እና ፋብሪካዉም የበኩል እንዲወጣ ጠይቀዉ በዉል ሂደቱም ሚና የነበራቸዉን አካላትም አመስግነዋል፡፡
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግርም 13ኛውን ውል በምንፈፅምበት ወቅት ባለፈው የውል ስምምነት ላይ የታዩ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ የተደረገበት መሆኑን ገልጸዉ የሽያጭ ዋጋ ከመጨመር ባሻገር የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ካለ ተነሳሽነት እና አርሶአደሮችም በባለቤትነት ስሜት የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዉ የምስራቅ ሸዋ ዞን ህ/ስ/ማ/ማ ኤጀንሲን ጨምሮ በድርድሩ የተሳተፉ አካላት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
የመርሃግብሩ ተሳታፊዎችም በዉሉ መፈረም የተሰማቸዉን ደስታ በመግለጽ ለአፈጻጸሙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
Exit mobile version