በአገራችን በተነደፈው ስትራተጂ መሰረት በተለያዩ ተቋማት እና ከተማዎች በመተግበር ላይ ያለውን የሌማት ትሩፋት ፖሊሲ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እንደ ተቋም በመቀበል የተረጂነት ስሜትን በማስወገድ በራስ አቅም ሰርቶ ለመለወጥ ካለው ራዕይ አንፃር የሌማት ትሩፋት ኮሚቴ እና ንዑስ ኮሚቴ በማዋቀር የከብት ማድለብ፣ የዶሮ እርባታ፣ እና የተለያዩ ፍራፍሬና አትክልቶችን በመትከል እንዲሁም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ለፋብሪካው ሠራተኛ ልምዱን በማጋራትና ሠራተኛውም በራሱ ግቢ ውስጥ እንዲተገበር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በጤና አገልግሎት መምሪያ በወንጂ ሆሰፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የእርሻ ማሳ ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎች (ማንጎ፣ አቦካዶ) እና አትክልቶችን (ሠላጣ፣ ካሮት፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም) በመትከል ጥሩ ጅማሮ እየታየ ሲሆን በዶዶታም የከብት ማድለብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በቀጣይም የወተት ላም ለማስገባት እና የንብ ማነብ ሰራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ፡፡ በአሁን ሰዓት ለምግብነት የሚውል ሠላጣ ለፋብሪካው ሠራተኛ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦ በመሸጥ ላይ ነው፡፡

Scroll to Top