Skip to content
Facebook
Twitter
Telegram
YouTube
Home
About us
Board Members & Teams
Profile
Products
Major product
By products
Co-products
Tender
Foreign
Local
Vacancy
wonji shoa sugar factory
About us
Board Members & Teams
By products
CO
Co-products
Foreign
Home
Jobs
Local
Major product
News
Products
Profile
Services
Tender
Vacancy
በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እህት ስኳር ፋብሪካዎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እህት ስኳር ፋብሪካዎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እህት ስኳር ፋብሪካዎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የመተሀራ፣ የከሰም እና የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጆች እና አመራሮች ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ፋብሪካው ከስኳር ምርት በተጨማሪ እየተገበረ ያለውን የሌማት ትሩፋት ስራ የሆኑትን የተጓዳኝ ምርት ሥራዎችን እና ፋብሪካው በራስ አቅም የገነባውን የመጠጥ ውሃ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡
የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን እንግዶቹን በመቀበል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ ፋብሪካው ከስኳር ምርት በተጓዳኝ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን በመስራት የፋብሪካውን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ፣ ሠራተኛው ምርቶቹን በአነስተኛ ዋጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ እና የስራ ዕድል በመፍጠር በተለያዩ የስራ ክፍሎች ያሉትን የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ወቅታዊ ሳይሆን በየመምሪያው በአቅድና ሲስተም ተዘርግቶ እየተሰራ ውጤታማ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከእህት ስኳር ፋብሪካ የመጡት እንግዶች በስራ ጉብኝቱ ላይ ላነሱት ጥያቄ በባለሙያዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማድረግ እና አስተያየት በመቀበል የፋብሪካውን የልምድ ተሞክሮ አካፍለዋል፡፡
እንግዶቹም በፋብሪካው እየተሰሩ ያሉትን የሌማት ትሩፋት ስራዎች በማየታቸው እንደተደሰቱ እና ከፋብሪካው ያገኙትን የልምድ ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይ በስራ ላይ ለማዋል እንዲሁም ከፋብሪካው ጋር ለወደፊት በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው ለተደረገላቸው ሙያዊ የልምድ ልውውጥ ፋብሪካውን አመስግነዋል፡፡
Scroll to Top