ለፋብሪካው የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የእውቅና ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ

የወንጂ ሸዋ ስኳር  ፋብሪካ የፍይናንስ መምሪያ 2016 በጀት  ዓመት  ሒሳብ  በፋሪካው  ታሪክ ከረጅም  ዓመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ  ሒሳብ  ነሀሴ 24 /2016 ዓም በመዝጋታቸው  እና ያለፋ ዓመታት የኦዲት ግኝቶች  ላይ በአጭር ጊዜ ማስተካከያ  በማድረግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሠራተኞች እና ሀላፊዎች እውቅና እና ሽልማት  በቢሾፍቱ ከተማ ኖራ ሪዞርት ተከናውኗል ።

 የፍይናንስ መምሪያ ሒሳብ በወቅቱ እንዲዘጋ እና ሌሎች ሥራዎች እንዲከናውን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉት  ከ 22 አመት በፊት በፍብሪካው  የፋይናንስ  ሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ የነበሩ እና  ለ 22 ዓመታት በአሜሪካ እና በተለያዩ  ሀገራት  ብሎም በአለም አቀፍ ተቋማት  በፍይናንስ ሀላፊነት ያገለገሉ  አቶ ለቤዛ አለሙ ናቸዉ ።

የፍብሪካዉ  ዋና ሥራ አስኪያጅ  አቶ ጀማል  አማን አቶ ለቤዛ አለሙ  የፍይናንስ አሠራር ወደ ተሻለ አፈጻጸም  እንዲመጣ ላደረጉት ድጋፍ  ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል። አክለውም በየደረጃው ላሉ የፋይናንስ ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበው የእውቅና እና ሽልማት ተሠጥቷቸዋል።

Scroll to Top