የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወንጂ /ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የመስክ ጉብኝት እና የፋብሪካዉ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ ዉይይት አድርጎ ግብረመልስ ሰጥቷል፡፡

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወንጂ /ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የመስክ ጉብኝት እና የፋብሪካዉ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ ዉይይት አድርጎ ግብረመልስ ሰጥቷል፡፡ ከጥር14 – 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመገኘት በፋብሪካዉ የመስክ ምልከታ ያደረጉት የም/ቤት አባላት የፋብሪካዉን የ6 ወራት አፈጻጸም የተመለከቱ ሲሆን ከፋብሪካዉ አመራሮች፣ሰራተኞች፣የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ዩኒየን ተወካዮች እና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተናጥል ወይይት አድርገዋል፡፡ በምልከታዉም የፋብሪካዉ የእርሻ ዘርፍ ፣የፋብሪካ ዘርፍ እና በተጓዳኝ ልማት ላይ የታዩ ለዉጦች የተመለከቱና ፋብሪካዉ በዝግጅት ምዕራፍ ያከናወናቸዉ ተግባራት በኦፕሬሽን ወቅት የራሱ የሆነ አዎንታዊ መልክ እንዲኖረዉ ማድረጉን በማንሳት፣በመንግስት የተያዙ ኢኒሼቲቮችንም ከመተግበር አንጻር በጥሩ ተምሳሌነት የሚነሳ ተግባር መፈጸሙን፣ቆሞ የነበረዉን ከረሜላ ፋብሪካ ወደ ምርት ማስገባቱ፣የተለያዩ የፋበሪካዉን ምርትና ምርታማነት ማሻሻል ላይ አዉንታዊ አስተዋጽዖ ያላቸዉ ማሽነሪና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት እየተደረገ ያለዉን ጥረት በመልካም ጎን የታየ ሲሆን ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር ያለዉ መልካም ግንኙነት የኢንዱስትሪዉን ሰላም ከማስጠበቅ አልፎ ማህበረሰቡ እንደ ራሱ ሃብት ፋብሪካዉን ማየት መቻሉን ማስጠበቅና ማስቀጠል እንደሚገባ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ በዉይይት ማጠቃለያ ላይ በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ኮሬ እንደገለጹት በሸንኮራ አገዳ ማሳዎች ምርታማነት ላይ የተጀመረዉ ጥረት አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣በፋብሪካዉ ይዞታ ላይ ያለውም ሆነ በአዉትግሮወርስ ሞዳሊቲ እየለማ ያለዉ ሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ከዚህ ጎን ለጎን ተጨማሪ ማሳዎችን ወደ ልማት ማምጣት ላይ የተጀመረዉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አጽዕኖት ሰጥቷል፡፡ በፋብሪካ ዘርፍም የሃይል ማመንጨት እና አጠቃቀም ላይ የታዩ ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ እንዲሰራ በማንሳት ሰራተኞች ጋር ያለዉን የረዥም ጊዜ የስኳር እዉቀት/ልምድ እንዲሁም የእኔነት ስሜት ማስጠበቅ ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ግብረምልስ ተሰጥቷል፡፡
በመርሃግብሩ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለን ጨምሮ የዘርፍ ስራ አስኪያጆችና ማኔጅመንት አባላት ከም/ቤቱ ለተነሱ ጥያቄና ገንቢ አስተያየት ምላሽ የሰጡ ሲሆን የመሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡
Scroll to Top