የፋብሪካው የልማት ሥራዎች አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገለጸ!!

የቀድሞው የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የወቅቱ የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፉሮ በቀታን ጨምሮ የአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያዎች በወንጂ ሽዋ ስኳር ፋብሪካ በመገኘት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ከፋብሪካው ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የሸንኮራ አገዳ ልማት፣ የፋብሪካ ዘርፍ የሥራ እንቅስቃሴዎች እና የተጓዳኝ ልማት ሥራዎች አፈጻጸም ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ወቅት እየታየ ያለው አጠቃላይ የልማት ሂደት አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስተያየት የሰጡት እንግዶቹ፣ በፋብሪካው እየታየ ባለው ለውጥ የተሰማቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያዎች በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ ከፋብሪካው ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
Scroll to Top