የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በተጓዳኝ ልማት ያደለባቸውን ኮርማዎች ለፋብሪካ የሥራ መሪና ሠራተኛ እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ለገና በዓል በመሸጥ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አደረገ፡፡
ፋብሪካው በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር በተጓዳኝ ልማት ካደለባቸው ኮርማዎች ውስጥ በ3 (ሶስት) ወር የዱቤ ክፍያ ከወር ደመወዛቸው እየተቆረጠ ገቢ እንዲሆን ለማድረግ ለፋብሪካው የሥራ መሪ እና ሠራተኛ ለገና በዓል በመሸጥ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ተደረገ፡፡
የፋብሪካው ማኔጅመንት ቲም በራስ አቅም የደለቡትን ኮርማዎች ለገና በዓል ለበርካታ የፋብሪካው የሥራ መሪ እና ሠራተኞች በዱቤ ሽያጭ በማቅረብ በዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የአካባቢው ማህበረሰብ እጅ በእጅ ገንዘብ ከፍለው እንዲገዙ ዕድሉ ስለተመቻቸላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡