Categories: 21/1/2023

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!

‎በኢትዮጵያ የስኳር ኢንደስትሪ ታሪክ ውስጥ ስሙ በደማቁ የሚነሳውና በቀዳሚነቱ የሚታወቀው አንጋፋው ስኳር ፋብሪካችን፣ ለዘመናት የቆየውን ልምድና ዝና መነሻ በማድረግ አሁንም በውጤታማነት ጉዞ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
‎ይህ ግዙፍ ተቋም ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ምርቶችን ለኢትዮጵያውያን በማቅረብ ረገድ የሚጫወተውን ሚና ዛሬም በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በትጋት እየሰራ ይገኛል።
‎ከእነዚህ ተወዳጅ ምርቶቻችን መካከል ደግሞ በህፃን አዋቂው ልብ ውስጥ ሰርፆ የቆየውና የብዙዎቻችን የልጅነት ጣፋጭ ትዝታ የሆነው “ደስታ ከረሜላ” ዋነኛው ነው። ፋብሪካችን ይህን ተወዳጅ ምርት በድጋሚ ወደ ገበያ እንዲመለስ ሲያደርግ፣ የቀድሞውን ተወዳጅ ጣዕም ከዘመናዊ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ጋር አጣምሮ በማቅረብ የደንበኞቹን እርካታ ለማረጋገጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ነው።
‎ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጀምሮ፣ በምርት ሂደትና እስከ ስርጭት ድረስ የምንከተለው እጅግ ጥብቅ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት ፍሬ አፍርቶ፣ ዛሬ በታላቅ ኩራት የምስራች ልናበስራችሁ እንወዳለን። የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የእውቅና የምስክር ወረቀት (Quality Certification) በይፋ ተቀብሏል። ይህ የምስክር ወረቀት የምርታችንን አስተማማኝነትና ለደንበኞቻችን ጤና የምንሰጠውን ከፍተኛ ዋጋ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያረጋግጥልን ነው።
‎ለጥራት ሁሌም ቅድሚያ የምንሰጠው የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ፣ ይህንን የአገር አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ ማግኘታችን ለቀጣይ ስራችን ትልቅ ስንቅ ይሆነናል። ጥራታችንን ሳናጓድል፣ ያንን የለመዳችሁትን ጣፋጭ የደስታ ከረሜላ በ9 የተለያዩ ተወዳጅ ጣዕሞች በላቀ ጥራት ለሁላችሁም ማድረሳችንን እንቀጥላለን። አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
‎ደስታ ከረሜላ – ትናንትም፣ ዛሬም ለጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን!
wssf

Recent Posts

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago