Categories: 21/1/2023

ፋብሪካዉ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ፋብሪካዉ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ::

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በፋብሪካዉ ክልል እና አጎራባች ቀበሌ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ104 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፣
ፋብሪካዉ ከተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ 66 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እና በትምህርታቸው የተሸለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዩኒፎርም፣መማሪያ ደብተርና የሴቶች የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በመርሃግብሩ የፋብሪካዉ የሰዉ ሃብት ስራ አመራርና አቅርቦት ዘርፍ ስራአስኪያጅ፣የዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ፣የፋብሪካዉ ሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ሊ/መንበርን ጨምሮ የወንጂ ወረዳ ሴቶች ማህበርና ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት እንዲሁም ድጋፍ የተደረገላቸዉ ተማሪዎችና የትምርት ቤቶች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የፋብሪካዉ ሰዉ ሃብት ስራ አመራርና አቅርቦት ዘርፍ ስራ አስኪያጅ፣የወንጂ ወረዳ ሴቶች ማህበር እና የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ንግግር አድርገዋል፡፡
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተክል ክፍል መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበርና የፋብሪካዉ ሰራተኞችም የገንዘብ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡
wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago