Categories: 21/1/2023

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማከናወን ይገኛል

በአገራችን በተነደፈው ስትራተጂ መሰረት በተለያዩ ተቋማት እና ከተማዎች በመተግበር ላይ ያለውን የሌማት ትሩፋት ፖሊሲ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እንደ ተቋም በመቀበል የተረጂነት ስሜትን በማስወገድ በራስ አቅም ሰርቶ ለመለወጥ ካለው ራዕይ አንፃር የሌማት ትሩፋት ኮሚቴ እና ንዑስ ኮሚቴ በማዋቀር የከብት ማድለብ፣ የዶሮ እርባታ፣ እና የተለያዩ ፍራፍሬና አትክልቶችን በመትከል እንዲሁም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ለፋብሪካው ሠራተኛ ልምዱን በማጋራትና ሠራተኛውም በራሱ ግቢ ውስጥ እንዲተገበር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በጤና አገልግሎት መምሪያ በወንጂ ሆሰፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የእርሻ ማሳ ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎች (ማንጎ፣ አቦካዶ) እና አትክልቶችን (ሠላጣ፣ ካሮት፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም) በመትከል ጥሩ ጅማሮ እየታየ ሲሆን በዶዶታም የከብት ማድለብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በቀጣይም የወተት ላም ለማስገባት እና የንብ ማነብ ሰራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ፡፡ በአሁን ሰዓት ለምግብነት የሚውል ሠላጣ ለፋብሪካው ሠራተኛ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦ በመሸጥ ላይ ነው፡፡

wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago