Categories: 21/1/2023

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አዲስ የሰው ሀብት አደረጃጀት መዋቅር ለመተግበር ከፋብሪካው ሠራተኛ ጋር ግንዛቤ የመፍጠር ውይይት አደረገ፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 496/2014 መሰረት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ለመላቀቅ እንዲያስችል ተቋማዊ የሪፎርም ፕሮግራሞችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋናነት በአዲስ መልክ የተሻሻለውን የሰው ሀብት አደረጃጀት ድርጅታዊ መዋቅር፣ የሠራተኞች የስራ ምደባ አፈፃፀም መመሪያ፣ በትግበራው ተስፋ ሰጪ በሆኑ ተጨባጭ የውጤት ማሳያዎች እና በተፈጠሩ የልማት ተግዳሮቶች ላይ ስትራቴጂ ነድፎ ሠራተኛውን ግንዛቤ በማስጨበጥ በተቋማዊ የገፅታ ግንባታ እና በሠራተኛው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ውይይት አደረገ፡፡ በተጨማሪም የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ባስተላለፉት መልዕክት በመከናወን ላይ ባለው ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ፕሮግራም የስራ ሀላፊዎች እና የማህበር አመራሮች ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው ተገቢውን ሠራተኛ ለተገቢው ቦታ በመስጠት በታሪክ አጋጣሚ የተሰጣቸውን የሀላፊነት ሚና በመጠቀም ተቋሙን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያሻግር መሆን እንዳለበት ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡       
wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago