Categories: 21/1/2023

በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ምርሃ ግብር ተከናወነ፡፡

በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ምርሃ ግብር ተከናወነ

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር አካል የሆነዉ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ስነስርአት እንደ ተቋም መንከባከብ የእኔም ግዴታ ነዉ በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናወነ፡፡በእለቱ የፋብሪካዉ ዋና ስራአስኪያጅ የሆኑት አቶ ጀማል አማን እንዲሁም የዘርፍ ስራአስኪጆችን ጨምሮ በየደረጃዉ ያሉ የስራ ሃላፊዎችና የፋብሪካዉ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ከወንጂ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊና የቀበሌ አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡በመርሃግብሩ ላይ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለተሰታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት ዛፍ በመትከላችን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀመሜታ አግኝተናል ብለዉ ችግኝ መትከል ብቻዉን ግብ እንዳልሆነና መንከባከብ እንደሚገባ በመግለፅ በቀጣይ 2017 ዓ.ም ምርት ዘመን እንደ ፋብሪካችን የተያዘዉን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የስራ ሃላፊና ሰራተኛ የበኩሉን ሚና መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በፋብሪካ ደረጃ ከ100ሺ በላይ የፍራፍሬ ፣ ቀርክሃ እና ለግንባታ የሚሆኑ ዛፎች ችግኝ ተከላ እንደሚከናወንና በዛሬዉ መርሃግብር በወንጂና ሸዋ ላይ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ ተከታታይ ቀናት በፋብሪካ እና በየመኖሪ ሰፈሮች እንደሚቀጥል ከወጣዉ መርሃግብር ለመረዳት ይቻላል፡፡

wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago