Categories: 21/1/2023

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የስራ መሪዎችና ሲኒየር ባለሙያዎች በእርሻ ዘርፍ  የተከናወኑ ስራዎችን ጎበኙ

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የስራ መሪዎችና ሲኒየር ባለሙያዎች በእርሻ ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን ጎበኙ፡፡

በፋብሪካው የ2017 ዓ.ም ምርት እቅድን ለማሳካት እየተደረገ የሚገኘዉን ዝግጅት አስመልክቶ በሸንኮራ አገዳ ማሳዎች ላይ በመዘዋወር የተጎበኘ ሲሆን በጉብኝቱ በድሬይኔጅ መስመሮች ጥገና የታየ ዉጤት ፣ የተጎዱ ማሳዎችን ከድሬይኔጅ በወጣ አፈር የማከም ስራ ያመጣዉ ዉጤት፣በእርሻ ዘርፍ የተከናወኑ የሌማት ትሩፋት የስራ እንቅስቃሴ፣ በተጓዳኝ ልማት የእንቁላል ዶሮዎች እርባታ ማእከል ፣የስንዴ ዘር ስራ፣ በከፍተኛ ጥረት የለማ የአዉት ግሮወርስ የሸንኮራ አገዳ ማሳዎች ቁመና ታይቶ ዉይይትም ተደርጎበታል፡፡ በመርሃግብሩ ከተሳታፊ ስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በተሰጠ አስተያየት አሁን የሚታየዉ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ቁመና የተያዘዉን የስኳር ምርት እቅድን ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን በደስታ እና በልበሙሉነት የገለጹ ሲሆን ለዚህ ተስፋ ሰጪ ስራ የስራ አመራር ቦርዱን እና ማኔጅመንቱን አመስግነዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ባስተላለፉት መልዕክት በእርሻ ዘርፍ ይህ በማሳ ላይ አምሮ የሚታየዉን የሸንኮራ አገዳ ሳይባክን ፋብሪካ መድረስ እንዳለበት በመግለጽ በፋብሪካ ዘርፍ በኩልም አስፈላጊ ዝግጅት እንዲደረግ እና የተያዘዉን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago