Categories: 21/1/2023

ከሸንኮራ አገዳ ማምረት ልማት ውስጥ ወጥተው ከነበሩ አርሶ አደሮች ጋር ወደ ልማት ለመመለስ  የመስክ ምልከታ እና ውይይት  ተደረገ፡፡

ከሸንኮራ አገዳ ማምረት ልማት ውስጥ ወጥተው ከነበሩ አርሶ አደሮች ጋር ወደ ልማት ለመመለስ የመስክ ምልከታ እና ውይይት ተደረገ፡፡

መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም የፋብሪካዉ ከፍተኛ አመራር ከአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳደርና ከወንጂ አ/ሸ/አ/አ/ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አርሶአደሮች ጋር ዉይይትና መስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡

የመስክ ምልከታው እና ዉይይቱ በቀድሞው ምስራቅ ሸዋ ዞን በአሁኑ መዋቅር በአዳማ ከተማ አስተዳደር ሥር የታቀፉ የአዋሽ መልካሳ ወረዳ ስር ያሉ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ የነበሩ እና  በተለያዩ ምክንያቶች ከአዉትግሮወርስ የሸንኮራ አገዳ ልማት የወጡ አርሶ አደሮችን ወደ ልማቱ ለመመለስ እንዲቻል ታስቦ በዶዶታ ክላስተር የለማ የሸንኮራ አገዳ ላይ  የተደረገ  የመስክ ምልከታ ነዉ ፡፡

 በመርሃ ግብሩ የፋብሪካዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን፣የአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደረጀ እና የዶዶታ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ አብደላ ጠደቻ ዉይይቱን በጋራ የመሩት ሲሆን የአዉትግሮወርስ ልማቱን የተመለከቱ  ጥያቄና አስተያየቶች ከተሳታፊ አርሶ አደሮች ተነስተዉ በአመራሮች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል በተለይ አርሶአደሩ ወደ ሸንኮራ ልማቱ እንዲመጣ በፋሪካዉና ዩኒየኑ መካከል የተደረገዉ 12ኛ ዉል ስምምነት አርሶአደሩን ይበልጥ የሚያበረታታ እንደሆነ እንዲሁም በዶዶታ ክላስተር የለማው አገዳ ከፍተኛ ምርት እንደሚሰጥ የሚጠበቅ እና አርሶ አደሩን የበለጠ ተጠቃሚ እንደያደርገው  ከተሳታፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

በመርሃግብሩ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣የአዋሽ መልካሳ ወረዳ አስተዳደርና የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ፣የዶዶታ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ፣የወንጂ አካባቢ ሸ/አ/አ/ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ከፍተኛ አመራሮች፣ከዶዶታ እና አዋሽ መልካሳ ወረዳ አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን በመጨረሻም አርሶአደሮችን ወደ ልማቱ ለመመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዋሽ መልካሳ ወረዳ በኩል ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር መነጋገር እንዲቻል አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባዉ ተጠናቋል፡፡

wssf

Recent Posts

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት

በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት በትውልድ አሻራ የተገነባ፣ የጥራት ምስክርነት: ‎‎የደስታ ከረሜላ ፋብሪካ የክብር ጉዞ!…

6 months ago

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር

‎በ 60 ዓመታት የኑሮ ሩጫ ውስጥ ቤተሰብ ከማስተዳደር ባሻገር በውጤታማ እና ስኬታማ የሥራ ዘመናት የተገነባ…

6 months ago

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!!

ጣፋጩ ደስታ ከረሜላ ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነዉ !!!! የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት የፋብሪካዉን…

1 year ago

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች  አክብሯል ::

አንጋፋዉ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የተመሰረተበትን የ70ኛ አመት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል :: ፋብሪካዉ  መጋቢት…

1 year ago